አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነዉ ተሾሙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ያቀረቡትን ሹመቶች ተቀብሎ አፅድቋል፡፡

በዚህ መሰረት አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፤ የአርባ ምንጭ ክላስተር አስተባባሪና የኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

አቶ ገ/መስቀል ጫላ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና በፌዴራል፣ በክልልና በየደረጃው በሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊነቶች ያገለገሉ መሆናቸዉ ተገልጿል።

በተጨማሪም በወላይታ ዞንና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት አቶ ዘብዴዎስ ኤካ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ የወረዳና የከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትም አፅድቋል።

Leave a Reply