የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ፤ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተከሰተ ያልተጠበቀ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን በአካል በመገኘት አጽናንተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፈጠረው አደጋ ህይወታቸው ላለፉት ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉም ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገዜ ጎፋ ወረዳ አደጋው በደረሰበት ቦታ በመገኘትም በአካባቢው ባህል መሰረት በማረፍያ ስፍራ ከርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ጋር የችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡
በክልላችን ጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ በከፍተኛ ሀዘን ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለማጽናናት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተጨማሪ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጋሾ፣ የመ/ኮሚንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።