መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት አመት የበጀት ዕቅድ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ባካሄደው በዚሁ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ/ም በጀት 37,600,566,984 (ሰላሳ ሰባት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊየን አምስት መቶ ስድሳ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት ብር) እንዲሆን ውሳኔ በማሳለፍ ለክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት እንድፀድቅ መርቷል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በክልሉ በበጀት አመቱ አላስፈላጊ ወጪዎችን መቀነስ እና የውስጥ ገቢን ማሳደግ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በጥልቀት በመወያያት አቅጣጫ አስቀምጧል።