የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ በእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ ከተማ በተለመዶው አሸዋ ገበያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቅርቡ በደረሰ የእሳት አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ ከተማ በነበራቸው የስራ ቆይታ በከተማው በቅርቡ በደረሰው የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልፀዋው፤ የከተማ አስተዳደሩ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የከተማ አስተዳደሩ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በክልሉ ህዝብ ስም የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን በመግለፅ ድጋፉን ለክቡር ከንቲባው አስረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እደተናገሩት የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የድሬ ህዝብ በችግራችንም ሆነ በልማታችን ሁሌም ከጎናችን ነው ያሉ ሲሆን፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አስተዳደሩ የአደጋው ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት በቀጣይም የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ርዕሰ መስተዳድሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች ስም ተጎጂዎችን ለማቋቋም ላደረጉት ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Reply