19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን፤ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በዓሉን ለማክበር የብልፅግና ቱርፋት ማሳያ፣ የጥበብ መፍለቂያ፣ የሠላምና የመቻቻል ተምሳሌት ወደ ህነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ኃሳብ በተከበረው በዓሉ፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የፍቅር ምንጭና የአንድነት መሰረት መሆን መቻሉን ተናግረዋል።
የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ የሩቅና የቅርብ ጠላቶችን ተስፋ በሚያስቆረጥ መልኩ በድምቀት በመከበር ላይ መሆኑንም በመልዕክታቸው ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ አለም የሚቀናባት የበርካታ ባህልና እሴቶች እንዲሁም የወብት መገለጫ ሀገር መሆኗንም ገልፀው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ልትጠፋ ነው የተባለች ሀገርን ከገደል አፋፍ በማንሳት እንድትቀጥል ማድረጉን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ውበትና ፀጋ የሚታደሉት እንጂ የሚታገሉት አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ፤ ኢትዮጵያን ተስፋ ያላትና አስተማማኝ ሀገር እንድትሆን አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ሀገራዊ ለውጡ ከይስሙላ ፌዴራሊዝም ወደ ዕውነተኛ ፌዴራሊዝም ያሸጋገረ እንዲሁም ነጠላ ትርክትን ወደ ብሔራዊ ትርክት በመቀየር ቱርፋት ነበረውም ብለዋል።
ወደ ብልፅግና ያሻገሩ ፈተናዎችን ወደ ኃይል ለለወጡት፣ የሀሳብ አፍላቂና የለውጡ ፋና ወጊ ለሆኑት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ላቅ ያለ ምስጋና ችረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ተምሳሌት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ክልሉ በተፈጥሮና በባህል የታደለ በመሆኑ ለሀገር የሚበጅ ምርታማነትን ያረጋግጣል ሲሉ ተናግረዋል።
ለዚህ ደግሞ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር እና ትብብርን ማጎልበት እንደሚገባ ገልፀዋል።