ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
የመስቀል በዓል ኃይማኖታዊ ትውፊት ያለው በዓል ቢሆንም በመላው ሀገራችን በጋራ በሁሉም ኢትዮጵያዊን የሚከበር በዓል ነዉ።
በዓለምአቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ ቅርሶች አንዱ በመሆኑም በዓለም ደረጃ እዉቅና ያለዉ ታላቅ ክብረ በዓል ነው፡፡
በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ያሸበረቀና የደመቀ ብቻም ሳይሆን በአዲስ ተስፋና ዕድልም የታጀበ ነው፡፡
ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ በአዲስ አስተሳሰብና ወኔ፣ በተሻለ ዕቅድና ዝግጅት ለለውጥ፤ ለእድገትና ለስኬት በምንዘጋጅበት ወቅት ላይ የሚከበር በዓል በመሆኑ መልካም በዓል እንድሆን እመኛለሁ።
በዚህ አጋጣሚም ለአዲሱ ክልላችን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና አስተዋፆ የሚያበረክቱ የወንድማማችነት/እህትማማችነት የሚያጠናክሩ አስተሳሰቦች የምንገነባበት ለዚህም ሁላችንም አበርክቶ የምናደርግበት እንድሆን ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሁም በጎነት በማሳየት፤ ፍቅር በመስጠት እና ቸርነት በማድረግ የምናከብረው በዓል እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
መስከረም 16/2016 ዓ/ም
ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር