“ለአንድ ወር በሚቆየው መፅሐፍ የመለገስና የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ ሁሉም በንቃት በመሳተፍ በክልሉ የጋጠመንን የመፅሃፍት እጥረት በማቃለለ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪ አስተላልፋለሁ “ርዕሰመስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ሀሳብ አመንጪነት እየተካሄደ የሚገኘው አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ የመፅሀፍ የማሰባሰብና የመለገስ መርሃ ግብሩ በመካሄድ ላይ ነው ።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለአንድ ወር በሚቆየዉ መፅሐፍ የማሰባሰብና የመለገስ ዘመቻ ላይ ሁሉም በንቃት በመሳተፍ በክልሉ በየደረጃዉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያጋጠመውን የመፅሀፍ እጥረት በማቃለል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል ።

መድረኩ ለትምህርት ስብራት ሁሉም መፍትሄ ከመፈለግና የራሱን አሻራ ከማሳረፍ ባለፈ በክልሉ የእስካሁኑ ጉዞና በቀጣይ እቅድ ላይ የሚመከርበት እንደሆነም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

የክልሉ ህዝቡ በማሳተፍ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት እንዲሆን ላማስቻል በእቅድ በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት መገኘቱን መከናወን መቻሉን አስረድተው በእቅድ በተያዙ ቀሪ ተግባራት ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት በ100 ቀናት እቅድ በማስደገፍ በልዩ ርብርብ ይሰራል ብለዋል ።

Leave a Reply