ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን በቡስካ ደብረ ጽዮን አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም የተገነባ የዕደ ጥበብ ውጤቶች ማምረቻ ማዕከል መርቀው ከፈቱ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን እያደረጉ ባሉት የስራ ጉብኝት፤ በደቡብ ኦሞና ኦሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት በቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማሪያም ዋአብነ ሙሴ ጸሊም ገዳም የተገነባ የተለያዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች ማምረቻ ማዕከል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ  ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክበረት ጋር በጋራ መርቀው ከፍተዋል፡፡  

ርዕሰ መስተዳድሩ በገዳሙ በቴክኒክና ጥገና ዘርፍ፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የዕደ ጥበብ ስራ ልማት፤ በግብርና እንዲሁም በስነፅሁፍና ቅንብር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትንም ጎብኝተዋል።

ገዳሙ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በመሰማራት አልባሳትንና ሌሎች የተለያዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች በማምረትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ ገቢውን ከማሳደጉም ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ገዳሙ ባጭር ጊዜ ውስጥ በአምራች ኢንዲስትሪው ዘርፍ በአልባሳትና ሌሎች የዕድ ጥበብ ውጤቶች ምርት የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቋቋት ላይ ከመሆኑም ባሻገር በአካባቢው ለአካቢብ ጥበቃና የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት የራሱን አስትዋጾኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡   

በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስቴር ሙዓዘ  ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክበረት እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply