ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኦሞ ዞን ገቡ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ማምሻውን ደቡብ ኦሞ ዞን ገብተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ መቀመጫ ዲመካ ከተማዋ ሲደርሱ በዞኑ አመራሮች እና በአከባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን፤ በቅርቡ በዳሰነች የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ያስከተለውን ጉዳት በአካል ተገኝተው በመመልከት በመፍትሄ ሀሳብ ዙሪያ ከዞኑ አስተዳደርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የሚመክሩም ይሆናል።

Leave a Reply