ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ ተገኝተው የጂንካ ከተማን የኮሪደር ልማት ስራ ጎብኝተዋል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የኣሪ ዞን  መቀመጫ የሆነችው ጂንካ ከተማ የገቡ ሲሆን፤ ለይፋዊ የስራ ጉብኝቱ ጂንካ ሲደርሱ፤ በዞኑ አስተዳደር አመራሮችና በከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። 

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኣሪ ዞን፣ ጂንካ ከተማ የሚገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ በጂንካ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ የከተማው አስተዳደር፣ የከተማውን ህብረተሰብ በማስተባበር እና የልማቱ ባለቤት በማድረግ በማከናወን ላይ የሚገኘውን የኮሪዴር ልማት ስራ አድንቀዋል።

በጂንካ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘው የኮርደር ልማት ስራ፣ የከተማዋን ገፅታ በመቀየር የጂንካ ከተማን ዕድገት በማፋጠን ላይ መሆኑ በጉብኝቱ ተመልክቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጉብኝቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፡- “ከተማዋ የፍቅር፤ የመቻቻል እና የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች፤ በነዋሪዎቿ ትብብርና ተሳትፎ በዕድገት ጎዳና ላይ ትገኛለች። ለዚህም የከተማው የልማት ስራዎችን ላስተባበራችሁ እና ለተባበራችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ጂንካዎች ትለያላችሁ፤ በርቱ!” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጂንካ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የችግኝ ተከላ አካናውነዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ማምሻውን የዲሽታ ጊና በዓል ዋዜማ ማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተውም፤ የበዓሉን ማብሰሪያ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ አብረው አክብረዋል።

ዋዜማው ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ፣ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባዉዲ እና ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በማርሸ ባንድ ታጅቦ ተከብሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጂንካ ቆይታቸው ሌሎች የልማት ስራዎችን የሚጉበኙ ከመሆኑም ባሻገር፣ በነገው ዕለት በልዩ ድምቀት በሚከበረው ዲሽታ ግና የኣሪ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል ላይ በመገኘት በዓሉን ከመላው ህዝብ ጋር የሚያከብሩም ይሆናል።  

Leave a Reply