ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን አጽናኑ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኮርያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ አቋርጠው በመመለስ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን አጽናንተዋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ፤ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የአደጋውን መከሰት ተከትሎ በደቡብ ኮርያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ አቋርጠው በመመለስ በጎፋ ዞን አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን አጽናንተዋል፡፡

Leave a Reply