ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱና የአደጋ ስጋት ያለባቸው ወገኖችን በዘላቂነት የማቋቋም ሥራው ያለበትን ደረጃ ጎበኙ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ እና የአደጋ ስጋት ያለባቸው ወገኖችን በዘላቂነት የማቋቋም ሥራው ያለበትን ደረጃ ጎበኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት፣ የክልሉ መንግስት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የማቋቋም እና የአደጋ ስጋት ያለባቸውን ከአደጋ ስጋት ነፃ የማድረግ ስራ አፅኖት ሰጥቶ በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የአደጋውን መከሰት ተከትሎ መላው ኢትዮጵያዊያን ከሁሉም አቅጣጫ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ መንግስት አፋጣኝ ድጋፍ የሚሹና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት በዘላቂነት የማቋቋም ሥራ በትኩረት በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ለ120 አባወራዎች ቤት በመገንባት እና ከነሙሉ ፓኬጅ በሟሟላት ኑሮ እንዲጀምሩ መደረጉን ገልፀዋል።

ለቀሪ አባወራዎች ቤት በመገንባት ላይ መሆኑን  የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ እስከ ሰኔ ግንባታው ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ በዘላቂነት በማቋቋም ኑሮ እንዲጀምሩ የሚደረግ መሆኑንም አብራርተዋል።

በአደጋው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ  ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረው፣ በቀጣይ አካባቢውን በግብርና ስራ በተለይ በሌማት ትሩፋት ሞዴል የማድረግ ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል።

Leave a Reply