
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ከሰላምና ፀጥታ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን በትኩረት ዳስሰዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው የክልሉ መንግስት ለሁሉም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት የተረጋጋ ሰላምና ፀጥታን ማስፈን ቁልፍ መሆኑን በማመን፤ በግማሽ የበጀት አመቱ በርካታ ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን ገልፀዋል፡፡



በተለይ የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በመሰብሰብ፣ በመተንተንና በማደራጀት የተለያዩ ፈጣን ምላሾችን መስጠትና የኃይል ግጭት ጉዳቶችን ትርጉም ባለው ልክ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
አክለው የሰላም ግንባታ ስራው ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ለማስቻል የኃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት እና እስከታችኛው መዋቅር የዘለቀ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በተደራጀ አግባብ በተሰሩ ስራዎች የክልሉን አንጻራዊ ሰላም ማጽናት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የላቀ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትንና ትብብርን በማረጋገጥ የተረጋጋ ሰላምና ጸጥታ ለማሰፈን ከአጎራባች ሀገራት፤ ከክልሎች እንዲሁም በዞኖች መካከል የሰላምና ፀጥታ የጋራ ፎረሞችን በመፍጠር ውጤታማ መኮኑንም ተናግረዋል።



ከዚህም ባሻገር ለክልሉ ሰላምና ፀጥታ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ በተለይ ለህገ-ወጥ መሳሪያ እና የአደገኛ ዕጽ ዝዉዉር ትኩረት ሰጥቶ የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር በርካታ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የኮንትሮባንድ ንግድ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር በትኩረት በተሰሩ ስራዎች ከ132 ሚሊዮን 748 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ከነተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
በሁሉም መዋቅሮች ህብረተሰቡን ያሳተፈ የአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ ስራዎችን ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በማከናወን እንዲሁም በሰላም፤ በብዝኃነትና በአብሮነት እሴት ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ተሞክሮ ሊቀመርባቸው የሚችሉ ውጤቶች መመዝገባቸውም ተመላክቷል፡፡