“ልመናን እና ዕርዳታ ጠባቂነትን እንደ ነውር የሚጸየፍ ማህበረሰብ በመገንባት በሥራ ምርታማነትን የሚያረጋግጥ ትውልድ፣ የሀገሩን ክብር የሚያስጠብቅ ዜጋ ለማፍራት የጀመርነውን ሁሉ አቀፍ ጉዞ መላው ሕዝባችን በቁጭት በመነሳት በሙሉ አቅሙ ሊደግፍ እና ሊያግዝ ይገባል።
ድሆች ነን፣ ያለ ድጎማና እርዳታ መለወጥና መበልፀግ አንችልም የሚል የጥገኝነት፣ የተረጂነት እና የጠባቂነት አስተሳሰብንና አመለካከትን በመስበር፤ በእጃችን ያሉንን ፀጋዎችና የመልማት አቅሞች በአግባቡ በመጠቀም ተባብረን በጋራ ተግተን ከሰራን፤ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ብልፅግናችንን በተሟላ ሁኔታ በእጃችን ማረጋገጥ እንችላለን።
ለዚህም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያችንን ተከትሎ በተለይ በግብርና ልማት፤ በበጋ ስንዴ፤ በሌማት ትሩፋት፤ በቱሪዝም፤ በኢትዮጵያ ታምርት፤ በሕዳሴ ግድብ፤ በአረንጓዴ አሻራ፤ በኮሪደር ልማትና ሌሎችም የጋራ ርብርብ በማድረግ እንደ ሀገር ባጭር ጊዜ ማስመዝገብ የቻልነው ተጨባጭ ለውጥ ማሳያ ነው”።
ለተሻለ ነገ ዛሬን ተባብረን ተግተን በኅብረት እንስራ!!
ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር