
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ያቀረቡትን የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሎ የቆዩት አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው ተሾመዋል፡፡
በዚህም አቶ ገብረመስቀል ጫላ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፡፡