እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
(መስከረም 15/ 2016 ዓ.ም) እንኳን ለ1 ሺህ 498 “የመውሊድ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ መውሊድ የመቻቻል፤የይቅርታና የመተባበር በዓል ነው ሲሉ ገልጸው የበዓሉ ቱሩፋቶችን በመጠቀም በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ መሳሪያ የሚሆነን የህዝባቸን አብሮነት እንዲጎለብት፤ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲያብብ ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አመላክተዋል፡፡
አክለውም ለሁላችንም በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሁም የተቸገሩትን በመረዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅ ያዘኑትን በማፅናናት እና ሌሎች የተቀደሱ ተግባራትን በመከወን የምናሳልፍ በዓል እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መልካም በዓል!
👏👏