አርባምንጭ ልባዊ ፍቅሯንና አክብሮቷን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጻለች

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝቱ አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱ በከተማው ኅብረተሰብ ከልብ የመነጨ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርባ ምንጭ የሀገራዊው የ’ገበታ ለትውልድ’ አካል የሆነው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በከተማው ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በደረሱበት የከተማው ጫፍ ሁሉ መላው የከተማው ኅብረተሰብ ልባዊ ፍቅሩንና አክብሮቱን ገልጾላቸዋል፡፡

በሀገሪቱ አርባ ምንጭ በተፈጥሮ ጸፀጋውና ባለው እምቅ የቱሪዝም አቅም ብቻ ሳይሆን በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት፤ ሰው አክባሪነት እና ልብ የሚሞላ ፍቅር ይታወቃል፡፡

Leave a Reply