
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ያቀረቡትን የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል፡፡


በዚህ መሰረት፡-
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የጂንካ ክላስት አስተባባሪ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዮት ዶክተር አበባየሁ ታደሰ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፡፡