ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ”ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከብሯል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሃ ግብሩ፤ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ በከፍሉት መስዋዕትነት ሉዓላዊነታችንና ህብረ ብሔራዊነታችን ተረጋግጧል ሲሉ ተናግረዋል።
ሰንደቅ ዓላማችን ከምንም በላይ ማን መሆናችንን የሚገልጽ፤ የነፃነትና የአንድነት ዓርማችን ነዉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ይህም እኛ ኢትዮጵያውያንን የመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል ሆነን በየትኛውም አለም ከፍ ብለን እንዲንታይ አስችሏል ብለዋል።
የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናስብ፤ ድህነትን ድል ነስተን፤ ብልፅግናችንን ዕውን በማድረግ ሉዓላዊነታችንን በሙላት ለማረጋገጥ በመነሳት መሆን እንዳለበትም ነዉ ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት፡፡