ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ የዘንድሮ የአርንጓዴ አሻራ መርሃግብርን ችግኝ በመትከል አስጀምረዋል።
የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መርህ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።
መንግስት እንደ ሀገር በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እንዲሁም የአፈር መሸርሸር እና የውሃ እጥበትን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያን የአካባቢ ደህንነትና የደን ሽፋን በማሳደግ ላይም ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘንድሮ ክረምት የአርንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚደረገው የቅድመ ተከላ ዝግጅት ቀደም ብሎ የተጠናቀቀ ሲሆን ችግኝ ተከላውን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በይፋ አስጀምረውታል።
በክልሉ በዘንድሮ የአርንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከ 372 ሚልየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል ታቅዶ ሲሳራ ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አርባ ምንጭ ሲደርሱ በርዕስ መስትዳድር ጥላሁን ከበደ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።