ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ( ዶ/ር)  በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሰላምበር ከተማ የስራ ጉብኝት አድርገዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ( ዶ/ር)  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን እያደረጉ ባሉት የስራ ጉብኝት ወደ ቁጫ ወረዳ በመጓዝ በሰላምበር ከተማ የስራ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚሁ የስራ ጉብኝት ሰላምበር ሲደርሱ በመላው የወረዳው ህዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰላምበር ቆይታቸው ለመላው ኢትዮጵያውያን ሰላም ከሰላምበር በማለት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሁሉም መሰረት የሆነው ሰላምን በጋራ ጠብቆ በማጽናት ለዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊተባበር ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰላምበር ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩ ሲሆን ወጣቱ ችግኝ ተክሎ ተንከባክቦ ማሳደግን ባህል በማድረግ አካባቢውን ሊቀይር እነደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት እጅግ የተደሰተው የአካባቢው ህዝብ ደስታውን፤ ፍቅሩንና ልባዊ አክብሮቱን በነቅስ ወጥቶ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾላቸዋል፡፡

Leave a Reply