“ጠንካራ ፓርቲ እና ጠንካራ መንግስት በመገንባት ሀገራችንን በአጭር ጊዜ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአባላት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ ከተናገሩት፡-

ጥያቄዎቻችን ሊፈቱ የሚችሉት ጠንካራ ፓርቲና መንግስት ሲኖረን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአባል ቁጥር፣ ጥራት እና ውጤታማነት የጠንካራ ፓርቲ መገለጫ እንደሆነ ጠቅሰው አባላት ፓርቲው ጠንክሮ ውጤት እንዲያመጣ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠንካራ ፓርቲና መንግስት ያለው ሀገር የህዝብን ፍላጎት በመለየት የልማት ጥያቄ መመለስ እንደሚችል አብራርተው፣ የክልላችንን ሰላም ማስጠበቅ አንዱ የጠንካራ ፓርቲና መንግስት መገለጫ መሆኑን በመጥቀስ የፓርቲው አባላት የሰላም አምባሳደር በመሆን የክልሉን ሰላም ይበልጥ ማስጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ልማት ሌላው የጠንካራ ፓርቲና መንግስት መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርና ስራዎቻችንን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ክረምቱን ትምህርት ቤቶችን ከመጠገን ጀምሮ የትምህርት ግባዓቶችን ለማሟላት መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ “በአንድ ወር-ለአንድ ተማሪ-አንድ መፅሃፍ” በሚል ሃሳብ የጀመርነው ንቅናቄ ላይ ሁሉም ዜጋ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ፍትሃዊ ግብር በመሰብሰብ የውስጥ አቅምን ማሳደግ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ቁልፍ መሆኑን አብራርተው ክልሉ ያለውን ፀጋ በመጠቀም ሀብት መፍጠርና የተሻለ ገቢ መሰብሰብ በልዩ ሁኔታ ሊታይ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎን ማጠናከር ሌላው የጠንካራ ፓርቲና መንግስት መገለጫ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በመስራት እንዲሁም ህዝባዊ ትስስርን በማጠናከር የህብረተሰብ ተሳትፏችንን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

ጠንካራ ፓርቲ እና ጠንካራ መንግስት በመገንባት እንዲሁም በህዝብ ተሳትፎ ፈተናን ወደ ድል በመቀየር ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን በትጋት መስራት ያስፈልጋል በማለት መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

Leave a Reply