የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ7ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

(ወላይታ ሶዶ መጋቢት 01/2016 ዓ.ም) መስተዳድር ምክር ቤቱ ዛሬ በበይነ መረብ ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ በተለይ ለክልሉ የኢንቨስትመንት ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ ክልሉ ካለው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት አቅም አንጻር ዘርፉ ለክልሉ ልማት እና ዕድገት በሚጠበቀው ልክ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችል ለማስቻል ቀጣይ የተግባር አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል።

Leave a Reply