ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ አንኳር ነጥቦች፡-
*የልማት ጉድለቶችን እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በመለየት እና የክልሉን አቅም መሠረት በማድረግ ይሰራል ።
*ክልሉ ያለውን ሀብት መለየት እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል የክልሉ መንግስት ትኩረት መሆኑን ያመለከቱ ርዕሰ መስተዳድሩ፤በልማት ስራዎች የኅብረተሰብ ተሳትፎን ማጠናከር እንደሚገባም አንስተዋል።
- ክልሉ ካለው አቅም አንፃር እየተሰበሰበ ያለው ግብር በሚፈለገው ልክ አለመሆን ገልጸዋል። ገቢን በአግባቡ ያለ ማሳወቅ፣ሕገ-ወጥ ደረሰኝ መጠቀም እና የገቢ ስወራ ችግሮች መኖራቸውን አመልክተዋል።
- ግብርናውን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ ተቋማዊ አሰራርን እስከ ቀበሌ ማጠናከር እና የግበዓት አቅርቦትን ማሻሻል በቀሪ ጊዜያት ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም አሁን ያለው የዝናብ ስርጭት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፤ የበልግ ልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት እንዲመራ አሳስበዋል።
*የንፁህ መጠጥ ውኃ ሽፋንን በተመለከተ፤ በገጠር 52 በመቶ ከነበረበት ወደ 57 በመቶ እንደዚሁም በከተማ 61 ከነበረበት 66 በመቶ ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
- የኤሌክትሪክ ኃይል ባላገኙ የክልሉ አካባቢዎች የኃይል አማራጮችን መሠረት አድርጎ ለማዳረስ ከሚመለከታቸው ተቋሟት ጋር የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ለምክር ቤቱ ገልፀዋል።
*ለአዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማት ፍላጎት እና ጥገና ጥያቄዎች በፌዴራል መንግስት የሚሰሩትን ጨምሮ በክልሉ የሚከናወኑ ስራዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ሊደረግ የሚገባቸውን በመለየት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥትን የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።