የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን፤ በዴንባ ጎፋ ወረዳ የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

በመረሃ ግብሩ ከብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተጨማሪ ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተው በመርሃግብሩ በመሳተፍ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።

ዘንድሮ ”የምትተክል አገር የሚያፀና ትዉልድ” በሚል መርህ ሃሳብ በመካሄድ ላይ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ በመጪው ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል፡፡

የዚሁ መርሃግብር አካል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 55 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply