
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረቡለትን የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ አጽድቋል።

በዚህ መሰረት:-
1ኛ.ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ
2ኛ.አቶ ተፈሪ አባተ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
3ኛ.ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ
4ኛ.አቶ ንጋቱ ዳንሳ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
5ኛ.ኢንጂነር ፍሬዘር ኦርካይዶ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
6ኛ.አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7ኛ.ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
8ኛ.አቶ ዳዊት ገበየሁ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
9ኛ.ወ/ሮ አፀደ አይዛ የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
10ኛ.ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለምክር ቤቱ ቀርበዋል።


የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት፤ በቢሮ ኃላፊነት እንዲሰሩ የቀረቡት ተሿሚዎች የካበተ ልምድ ያላቸው በመሆኑ ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንንት ሊያገለግሉ እንደሚገባ በማሳሰብ፤ የቀረበውን ሹመት በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።






ተሿሚዎቹ ከህዝብና ከመንግስት የተሰጣቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ለመፈጸም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል።
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ አቅራቢነት የ43 ዕጩ ዳኞች ሹመት ጸድቋል።


ከተሻሚ ዳኞች መካከል 20ዎቹ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲሆኑ ቀሪዎቹ ለዞን ፍርድ ቤቶች የተሾሙ ናቸው።
ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በስኬት አጠናቋል።