
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ የሰላምና ፀጥታ ሰራዎች የተለያየ ድጋፍና እገዛ ሲያደርጉ ለቆዩ የመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ መኮንኖች እና ጄነራሎች በጽ/ቤታቸው እውቅና ሰጥተዋል።



ርዕሰ መስተዳድሩ በዕውቅና አሰጣጥ መርሃግብሩ ጀነራል መኮንኖቹ በክልሉ የፀጥታ ስራ የተለያዩ እገዛዎችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጾኦ ማበርከታቸውን ገልፀዋል።
የክልሉ መንግስት ክልሉን የሰላም፥ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በማድረግ ላይ ባለው ጥረት ዘርፈ ብዙ የሰላምና የፀጥታ ስራዎችን ማከናወኑን እና በማከናወን ላይ መሆኑን አያይዘው አብራርተዋል።


አክለው በተሰሩ ስራዎች በክልሉ የተረጋጋ የፀጥታ ሁኔታና አንጻራዊ ሰላም በስኬት ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀው፥ በሂደቱም እኚሁ ከመከላከያ ሚንስቴር የመጡ ጀነራሎች የጎላ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻም ጀነራል መኮንኖቹ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ በቅንነት፣ በታማኝነትና በልባዊ መሰጠት በመስራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ ለ:-
1) ብ/ጄ ሰብስቤ ዱባ
2) ብ/ጄ አስፋው ማመጫ
3) ኮለኔል የሽዋስ ደምሴ
የምስጋና የምስክር ወረቀት እና ዕውቅና ሰጥተዋል።