“መጪው ጊዜ በተገኙ ስኬቶች መኩራራት የሚፈጠርበት ሳይሆን ከሀሳብ ልዕልና ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመሸጋገር ለቀጣይ ጉዞ ስንቅ የሚሆኑ አቅሞች ላይ በትኩረት የሚሰራበት መሆን ይኖርበታል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ”የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከብሯል፡፡ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ ከገጠመን የከፋ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ…