ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ፤ በጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ በአካባቢው ካለው የዝናብ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት በመደረግ ላይም ይገኛል፡፡…