Category Press Statements

Press Statements

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የፀጥታ ስራዎች በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጡ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ ባለፈው አንድ ወር ዉስጥ በፀጥታ ግብረሃይል የተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ከፀጥታ ኃይሎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ክልሉን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት፤ የፀጥታ ስራዎችን በህብረተሰቡ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በ17ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በወላይታ ሶዶ ከተማ ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው በልዩ ልዩ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በ17ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉን የ2017 የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫዎች በተመለከተ፤ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን…

በየደረጃው ያለው አመራር የተሰጠውን ከፍተኛ ኃላፊነትና ከህዝብ የተቀበለውን አደራ በአግባቡ በመወጣት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ ርብርብ ሊያደርግ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ “የህልም ጉልበት፣ ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝው መልዕክት በማስተላለፍ፤ ቀጣይ የስራ ስምሪት ሰጥተዋል፡፡   ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በክልሉ በየደረጃው ያለው አመራር የክልሉ መንግስት የሰጠውን ከፍተኛ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል – ተረጂነትን ታሪክ በማድረግ ጉዞ ላይ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተረጂነት እሳቤ የተላቀቀ ማህበረሰብ በመገንባት እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናንና ብልፅግናን በማረጋገጥ የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለመጎናፀፍ ለተያዘው ሀገራዊ ግብ ስኬት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡   የክልሉ መንግስት ለግብርናው ልማት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት፤ በ2015/16 የምርት ዘመን…

ተባብረን በጋራ ተግተን ከሰራን የሚያቅተን ነገር አይኖርም!

“ልመናን እና ዕርዳታ ጠባቂነትን እንደ ነውር የሚጸየፍ ማህበረሰብ በመገንባት በሥራ ምርታማነትን የሚያረጋግጥ ትውልድ፣ የሀገሩን ክብር የሚያስጠብቅ ዜጋ ለማፍራት የጀመርነውን ሁሉ አቀፍ ጉዞ መላው ሕዝባችን በቁጭት በመነሳት በሙሉ አቅሙ ሊደግፍ እና ሊያግዝ ይገባል። ድሆች ነን፣ ያለ ድጎማና እርዳታ መለወጥና መበልፀግ አንችልም…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የተገነባ የሳሙና እና የቅባት ፋብሪካ መርቀው በመክፈት በይፋ ሥራ አስጀምረዋል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን፤ ቦዲቲ ከተማ በማኑፋክቼሪንግ የኢንቨስትመንት ዘርፍ በተሰማራ የግል ባለሀብት የተገነባ “ኤ ኤንድ ቲ” የሳሙና እና ቅባት ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው በመክፈት በይፋ ሥራ  አስጀምረዋል።   ፋብሪካው በወጣት ባለሀብት አቶ አብርሃም ፋንታ እና ባለቤቱ…

ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ በዳሰነች ወረዳና በአካባቢው በክረምት ወቅት በተደጋጋሚ የሚከሰት የጎርፍ አደጋ በጥናት ላይ በተመሰረተ አግባብ በዘላቂነት ለመፍታት ይሰራል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ የተከሰተ የጎርፍ አደጋ በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን፤ በአደጋው ዙሪያ በኦሞራቴ ከተማ ከአካባቢው ህብረተሰብ ተወካዮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡   ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይት መድረኩ የኦሞ…

ጥላቻን በፍቅር፤ ጥርጣሬን በእምነት በመቀየር የህዝብ ለህዝብ ትስስራችንን ይበልጥ አጠናክረን ለክልላችን ዕድገት እና ለህዝባችን ሁለንተናዊ የጋራ ተጠቃሚነት ሊንረባረብ ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንደኛ አመት ታሪካዊ የምስረታ ክብረ በዓል “ከነሐሴ እስከ ነሐሴ” በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡     የክብረ በዓሉ አካል የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ “ከነሐሴ እስከ ነሐሴ” በሚል ርዕስ የክልሉን ምስረታ ሂደት እና…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን የመደገፍ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎች በትኩረት በማከናወን ላይ ይገኛል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከኢፕድ ጋር በነበራቸው ሰፋ ያለ ቆይታ የክልሉ መንግስት በመሬት ናዳና በጎርፍ አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ 19ሺ 847 ዜጎችን የመደገፍ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በዚህ ክረምት ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የደረሱ የመሬት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ በአንድ ጀንበር ተከላ ለተመዘገበው አስደናቂ ስኬት ለመላው የክልሉ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዛሬው ዕለት በተከናወነው የሀገራዊው የአርንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 55 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ፤ ከዕቅድ በላይ 64 ሚሊዮን ችግኝ መትከል መቻሉን በመግለፅ ለመላው የክልሉ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክተቻው…