በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃ ግብር 55 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ከ64 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ ተችሏል
“የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ሀገራዊው የአርንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን፤ ሁምቦ ወረዳ ተገኝተው አሻራቸውን በማኖር በይፋ ያስጀምሩት ሲሆን፤ ተከላው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በአመራሩ አስተባባሪነት እና በህዝቡ…