ለጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች እሰካሁን 92 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና ከ118 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ መደረጉ የታወቀ ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ተጎጂዎችን ለመደገፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ በተለይ መላ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉ ባሉት ርብርብ ለአደጋው ተጎጂዎች አስፈላጊ የስብዓዊ ድጋፎችን በአግባቡ ማቅረብ ተችሏል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተጎጂዎችን የመደገፍና በዘላቂነት የማቋቋም…