Category Press Statements

Press Statements

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት የ2017 በጀት 37.6 ቢሊየን ብር አፀደቀ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ተወስኖ የቀረበለትን የክልሉን መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አስመልክቶ በጥልቀት ተወያይቷል፡፡ ምክር ቤቱ በመስተዳድር ምክር ቤት የቀረበውን የክልሉን መንግስት የ2017 ረቂቅ…

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ለዞን አስተዳደር እርከኖች ለ2017 በጀት አመት 30 ቢሊየን ብር በጀት እንዲመደብ ውሳኔ አሳለፈ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የ2017 በጀት በተመለከተ ከዞን አስተዳደር እርከን አመራሮች ጋር በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችና የመልማት ፍላጎቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ በ2017 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል የክልሉን ድርሻ በእጅጉ በመቀነስ የዞኖችን ድርሻ ከፍ ለማድረግ በመስተዳድር…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት አመት የበጀት ዕቅድ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ ባካሄደው በዚሁ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ/ም በጀት 37,600,566,984 (ሰላሳ ሰባት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊየን አምስት መቶ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወላይታ ሶዶ ከተማ ያካሄደ ሲሆን፤ በስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም እና በ2017 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በዋናነት የበጀት አመቱን የክልሉ መንግሰት አጠቃላይ የስራ…

“ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈል ሀገርን የማልማት እና የመገንባት የሚያኮራ የዜግነት ተግባር ነው!”  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅትን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ግብር የተጫነብን ግደታ ሳይሆን እንደ ዜጋ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት የምንፈጽመው የሚያኮራ የዜግነት ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡ ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈላችን እንደ ዜጋ ለሀገራችን ልማት የድርሻችንን…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ ዘንድሮ ለገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ከመቸውም ጊዜ በላይ የገቢ አሰባሰብ ስራዉ በተደራጀ እና በተቀናጀ አግባብ…

“ገበታ ለትውልድ በምድረ ገነቷ አርባምንጭ ለመላው ኢትዮጵያውን ዕድል ይዞ ቀርቧል” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በከተማው በማድረግ ላይ ያሉትን የስራ ጉብኘት አስታከው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም አርባ ምንጭ የፍራፍሬ ቅርጫት ከመሆኗም በላይ…

ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ የዘንድሮ የአርንጓዴ አሻራ መርሃግብርን ችግኝ በመትከል አስጀምረዋል። የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መርህ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል። መንግስት እንደ ሀገር በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እንዲሁም የአፈር መሸርሸር…

በደቡብ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ ክልሎች ቀጠናዊ የሠላምና ፀጥታ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ ምክክር ተካሄደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ፣ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና በመከላከያ ሚኒስትር የደቡብ እዝ አዛዥ ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ እና በኦሮምያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ቀጠናዊ ሠላምና ፀጥታ ዙሪያ የጋራ ምክክር በአርባምንጭ ከተማ…

የክልሉ መንግስት ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 1 ሺህ 455 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ርዕሰ…