News

በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የ “አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ” ኢንሼቲቭ ከኅብረተሰቡ በተሰበሰበ ሀብት የታተሙ መፅሐፍት ሥርጭት ተጀመረ

በርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ ሃሳብ ጠንሳሽነት ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ በቆዬው ለመፅሐፍ ህትመት የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ዘመቻ በተሰበሰበ የገንዘብ ድጋፍ የታተሙ መፅሐፍት ሥርጭት ተጀመረ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት የሥርጭት ማስጀመሪያ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንደኛ ዓመት ምሥረታን በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ለመላው የክልሉ ሕዝቦች እንኳን ለታሪካዊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንደኛ ዓመት ምሥረታ አደረሳችሁ፤ አደረሰን ያሉ ሲሆን፤ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡- እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 1ኛ ዓመት ምሥረታ አደረሰን! አደረሳችሁ! ነሐሴ 13 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፌደሬሽኑ 12ኛው ክልል…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀምበር ከ4 ሺህ 5 መቶ በላይ በቶችን ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን መገንባትና ማደስ ተችሏል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተጀምሮ፤ በሁሉም የክልሉ ማዕከላት በተካናወኑ መርሃ-ግብሮች በልዩ ትኩረት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡ ፍፁም ሰው ተኮር በሆነው መርሃግብሩ፤…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ በእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ ከተማ በተለመዶው አሸዋ ገበያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቅርቡ በደረሰ የእሳት አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ ከተማ በነበራቸው የስራ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአርባምንጭ ከተማ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባው ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በመታየት ላይ ባለው ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ፤ በክልሉ የአደጋ ስጋት ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦች ላይ በጥልቀት በመመከርና በመወያየት ውሳኔ…

ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ አባላት ጋር በኢንቨስትመንት ዙሪያ ተወያዩ

ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቨስትመንት አቅም ዙሪያ ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ አባላት  ጋር  በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ የክልሉ መንግስት የክልሉን ዕድገት እና ልማት ለማፋጠን ልዩ ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ የኢንቨስትመንት ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ…

የክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ የዘላቂ ልማት እና የሠላም ዋስትና ማረጋገጫ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻ አካል ለዉጤታማነቱ ተቀናጅቶ በቁርጠኝነት መስራት ይገባዋል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንተርፕራይዞች ልማት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ “የክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ 2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል።   መድረኩ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካዎ ኮይሻ ወረዳ የመሬት ናዳ አደጋ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ከወላይታ ዞን ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ይገኛል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ለአደጋው ተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከወላይታ ዞን አስተዳደር ጋር በቅርበት በመስራት…