News

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በስፍራው በመገኘት አጽናንተዋል።  በክልሉ ወላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ርዕሰ…

ለጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች እሰካሁን 92 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና ከ118 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ መደረጉ የታወቀ ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል   

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ተጎጂዎችን ለመደገፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ በተለይ መላ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉ ባሉት ርብርብ ለአደጋው ተጎጂዎች አስፈላጊ የስብዓዊ ድጋፎችን በአግባቡ ማቅረብ ተችሏል፡፡     ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተጎጂዎችን የመደገፍና በዘላቂነት የማቋቋም…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ፤ በጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ በአካባቢው ካለው የዝናብ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት በመደረግ ላይም ይገኛል፡፡…

ከደረሰብን ልብ ሰባሪ ሐዘን በመውጣት በአስከፊ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም መረባረብ አለብን -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ   

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የታወጀው ብሔራዊ ሐዘን ቀን ማጠቃለያ ሻማ የማብራት ስነ-ስርዓት በሳውላ ከተማ ተካሂዷል፡፡   በክልሉ ጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ…

የክልሉ መንግስት በአደጋው የተጎዱና የተፈናቀሉ ወገኖችን በጥናት ላይ በተመሰረተ አግባብ በቋሚነት ለማቋቋም በመስራት ላይ ይገኛል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። አደጋው በስፍራው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የክልሉ መንግሥት የአፋጣኝ የነፍስ አድን ስራና የሰብዓዊ…

የደረሰብን ሀዘን ልብ ሰባሪና መላ ኢትዮጵያዊያንን ያሳዘነ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን በቦታው ተገኝተው ሀዘናቸውን በመካፈልና በማጽናናት መልዕክት አስተላልፈዋል።  ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አስከፊ ጉዳት ቦታው…

ኢትዮጵያ እና መላ ኢትዮጵያዊያን ከጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂ ወገኖቻችንና ከመላው የክልላችን ሕዝቦች ጋር ብሔራዊ ሐዘን ተቀምጠዋል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የተከሰተ ያልተጠበቀ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የመላ ኢትዮጵያዊያንን ልብ የሰበረ፤ የክልላችንን ህዝቦች በፅኑ የሐዘን ዳዋ የመታ አስከፊ ጥፋት ደርሷል፡፡ አደጋውን ተከትሎ የኢፌዴሪ…

የኢፌድሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች አጽናንተዋል

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ፤ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተከሰተ ያልተጠበቀ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን በአካል በመገኘት አጽናንተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፈጠረው አደጋ ህይወታቸው ላለፉት ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ…