እንደ ‘ዲሽታ ጊና’ ያሉ በክልሉ የሚገኙ ባህላዊ እሴቶች ለህዝቦች አብሮነት፣ ሰላምና ዕድገት ትልቅ አቅም በመሆናቸው በአግባቡ ጠብቆ በማቆየት መጠቀም ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ዲሽታ ግና፤ የኣሪ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በኣሪ ዞን መቀመጫ በሆነችው ጂንካ ከተማ በልዩ ድምቀት ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ዲሽታ ግና ለኣሪ ብሔረሰብ በኩር እና ታላቅ በዓል ነው…