News

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር በክልሉ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃ ግብርን በይፋ አስጀምረዋል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የሀገራዊው የአርንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን፤ ሁምቦ ወረዳ ጋልቻ ቃራ ቀበሌ ችግኝ ተክለው አሻራቸውን በማኖር በይፋ አስጀምረዋል።     ርዕሰ መስተዳድሩ መርሃግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት…

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጎፋ ዞን፤ በዴንባ ጎፋ ወረዳ የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል ችግኝ…

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በጎፋ ተገኝተው በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በማፅናናት ፓርቲው ተጎጂዎችን ለማቋቋም ያደረገውን የ20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አስረክበዋል

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የፓርቲው ከፍተኛ የአመራሮች ልዑክ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በማፅናናት የ20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።    ድጋፉን…

በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የ “አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ” ኢንሼቲቭ ከኅብረተሰቡ በተሰበሰበ ሀብት የታተሙ መፅሐፍት ሥርጭት ተጀመረ

በርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ ሃሳብ ጠንሳሽነት ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ በቆዬው ለመፅሐፍ ህትመት የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ዘመቻ በተሰበሰበ የገንዘብ ድጋፍ የታተሙ መፅሐፍት ሥርጭት ተጀመረ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት የሥርጭት ማስጀመሪያ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንደኛ ዓመት ምሥረታን በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ለመላው የክልሉ ሕዝቦች እንኳን ለታሪካዊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንደኛ ዓመት ምሥረታ አደረሳችሁ፤ አደረሰን ያሉ ሲሆን፤ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡- እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 1ኛ ዓመት ምሥረታ አደረሰን! አደረሳችሁ! ነሐሴ 13 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፌደሬሽኑ 12ኛው ክልል…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀምበር ከ4 ሺህ 5 መቶ በላይ በቶችን ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን መገንባትና ማደስ ተችሏል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተጀምሮ፤ በሁሉም የክልሉ ማዕከላት በተካናወኑ መርሃ-ግብሮች በልዩ ትኩረት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡ ፍፁም ሰው ተኮር በሆነው መርሃግብሩ፤…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ በእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ ከተማ በተለመዶው አሸዋ ገበያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቅርቡ በደረሰ የእሳት አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ ከተማ በነበራቸው የስራ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአርባምንጭ ከተማ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባው ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በመታየት ላይ ባለው ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ፤ በክልሉ የአደጋ ስጋት ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦች ላይ በጥልቀት በመመከርና በመወያየት ውሳኔ…