በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በተደረጉ ጥረቶች በህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተሳትፎ አበረታች ውጤት ማግኘት ተችሏል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ  

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት ክልላዊ የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በኦሪ ዞን ጂንካ ከተማ ተካህዷል፡፡  

”ትምህርት ለትውልድ ግንባታ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ጉባኤው፤ የበጀት ዓመቱ ያለፉ ዘጠኝ ወራት የትምህርት ዘርፍ የስራ አፈጻጸም ጨምሮ በክልላዊ የትምህርት ልማት ስራዎች፤ ተግዳሮቶች እና የትምህርት ዘርፉን የማጠናከር እንዲሁም የትምህርት ጥራትን የማሻሻል ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካህዷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት፡- ትምህርት የአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚ የበኩር አጀንዳ መሆኑንን ገልፀው፥ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው እድገት በማስመዝገብ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ትምህርት ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እንደ ሀገር በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው “የትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በርካታ ለውጦችን ማምጣት መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት እንደ ሀገር ያጋጠመን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በሚደረገው ጥረት፤ የትምህርት ተደራሽነትን ከማሳደግ ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡            

በተለይ ለትምህርት ጥራት መጠበቅ መሠረት የሆኑ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን የማሻሻል እና በየዕርከኑ ያሉ ትምህርት ቤቶችን በግብዓት የማጠናከር ስራዎች በህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተሳትፎ በትኩረት በመስራት አበረታች ውጤት ማግኘት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ 

ትምህርት የተሻለ ትውልድ በመቅረጽ የዛሬ ሀገር ገንቢዎችንና በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የታነፁ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን የማፍራት ታላቅ ተግባር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለዘርፉ ውጤታማነት የህብረተሰቡ እንዲሁም የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በክልሉ የህብረተሰቡ የትምህርት ዘርፍ ተሳትፎ በተለይም ትምህርት ቤቶችን በመጽሐፍትና ሌሎች ግብዓቶች የማጠናከር፤ የማደስና አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ መሆኑንም ገልፀው፤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ 

ይሄው የህብረተሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ ላይ ተጨባጭ ውጤት በማምጣት ላይ መሆኑ ባለፉ ጊዜያት በክልሉ የአንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ ኢንሼቲቪ እና በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተመዘገቡ ውጤቶች ማሳያ መሆናቸውንም አያይዘው ገልፀዋል።

ለዚሁ ስኬት የተረባረቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን አመስግነው አሁንም በመፅሃፍ ተደራሺነት ፣ በተማሪ ምገባ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡   

ትምህርት ለማህበራዊ ብልፅግና ትልም ስኬት መሠረት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የዘርፉ ውጤታማነት በተለየ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ፤ ድጋፍና ትብብር የሚፈልግ በመሆኑ በቀጣይም የትምህርት ዘርፍ ተሳትፎን ባህል በማድረግ ለውጤታማነቱ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሀይ ወራሳ በበኩላቸው፤ በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመረው የአንድ መፅሃፍ ለአንድ ተማሪ ኢኒሼቲቭ በርካታ ችግሮችን መቅረፍ የቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

የትምህርት ዘርፍ በርካታ መሻሻሎች ቢኖሩትም አሁንም መቀረፍ ያለባቸው ችግሮች መኖራቸውን ገልፀው፤ በተቀናጀ ርብርብ ዘርፉን ለማሻሻል መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

Leave a Reply