ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከወጣቶች ጋር እያደረጉት ባለው ውይይት በልማት፣ መልካም አስተዳደር፣ ስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥዋል
ርዕሰ መስተዳድሩ በምላሸቸው ሀገር አዲስ ለውጥ በጀመረች ወቅት ለውጡን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አፍራሽ ኃይሎች እና የተለያዩ የተፈጥሮ ሰው ሰራሽ ፈተናዎቾ በገጠመን ወቅት ወጣቶች ህዝብን በማደራጀት ድጋፍ በማሰባሰብ ብቻ ሳይሆን መስዋት በመሆን ጭምር ዋጋ መክፈላቸውን አስታውሰው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚደራጅበት ወቅትም በርካታ ፈተናዎች የታላፉት ወጣቱን በመያዝ መሆኑን በመግለጽ ወጣቶች በአጠቃላይ ለሀገር የከፈላችሁት ዋጋ ስማችሁን በደማቅ አሻራ የፃፈ አኩሪ የጀግነት ተግባር ነው በማለት ምስጋና አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እንደ ሀገር ትልቁ ጠላት ድህነት እና ኃላ ቀርነት እንደሆነ ጠቅሰው ወጣቱ ሀገራዊና ክልላዊ ተልኮዎች ሲሰጡት በአርበኝነት በመወጣት ድህነትን ታሪክ ማድረግ መቻል አለበት ብለዋል።
በለውጡ ሂደት በተመዘገቡ ድንቅ ስኬቶች የወጣቶች ድርሻ ከፍ ያለ እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ቀጣይ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ወጣቱ እድልን ወደ ወደ ድል እዳን ወደ ምንዳ መቀየር መቻል እንዳለበት በአፅኖት አሳስበዋል።
ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ወጣቱ በተለይ የሀገር ሰላም እና አንድነት ላይ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበው ሰላም የሚያደፈርሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ነገሮችን በመነጋገር የመፍታት ልምድን በማደበር የሰላም አምባሳደሮችና አርበኞች መሆን ይገባል ብለዋል።