የምግብና ስርዕተ ምግብ ዋስትናና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የምግብና ስርዕተ ምግብ ዋስትናና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልክታቸው፡-

በክልላችን ቀዳሚ የትኩረት መስክ በሆነው ግብርና የቴክኖሎጂና ግብዓት አጠቃቀምን በማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ አሰራሮችን በማላመድ ዘርፉን ለማዘመንና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የምግብና ስርዕተ ምግብ ዋስትናና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው፤ የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑ ታወቆ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለይ በመኸር እርሻ ያስመዘገብነውን አመርቂ ውጤት በበልግ አዝመራ ሥራችን በመድገም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የጀመርነውን ሽግግር ለማፅናት አመራሩ ከወዲሁ ቀድሞ በመዘጋጀት በልዩ ትኩረት መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

ለታለመው የበልግ አዝመራ ግብ ስኬት ጠንካራ የአመራር ሥርዓት እስከታችኛው መዋቅር በመዘርጋት፤ የበልግ ስራዎችን እንዲሁም የሌማት ትሩፋትና የአረንጓዴ አሻራ ተግባራትን እና ሌሎችም ኢንሼቲቮች አመራሩና ባለሞያው በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ በመምራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲሰሩ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply