ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአርባ ምንጭ ከተማ እያስገነባ የሚገኘውን የአረጋዊያን ማዕከል ጎበኙ

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት በጎ ማሰብና በጎ መስራት ለራስ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ሰው አቅሙ በፈቀደ መጠን በበጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ የተሻለ ማህበረሰብን ለመገንባት የድርሻውን ላበረክት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ይህን በመሰለ የማህበራዊ ቀውስን ለመቀነስ የሚረዳ ታላቅ ተግባር ላይ ሀብታቸውን፤ እውቀታቸውን እና ጊዜያቸውን በነፃ እየሰጡ ላሉ በጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ አርቲስቶችና ሌሎችም ከፍ ያለ ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአርባ ምንጭ ከተማ እያስገነባ የሚገኘው የአረጋዊያን ድጋፍና እንክብካቤ ማዕከል በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር ለማስቻል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት ሜሪጆይ ኢትዮጵያ በአርባ ምንጭ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋዊን መርጃ ማዕከል የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አጋር የሆነችው አንጋፋዋ ደራሲ ሜሪ ጃፋር ከአያቶቿ የወረሰችውን 400 ሺ ብር የሚገመት 24 ካራት ወርቅ በጨረታ ቀርቦ ለማዕከሉ ግንባታ እንዲውል በስጦታ መልክ አበርክታለች።

የክልሉ መንግስት በክልሉ የበጎ ስራዎች ላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በንቃት በመሳተፍ ዘርፍ ብዙ የድጋፍ እና ልማት ስራዎችን ለመስራት አቅዶ  በመስራት ላይ ይገኛል።

Leave a Reply