“ፓርቲው አዲስ ክልል በአዲስ እሳቤ በሚል መርህ ክልላችንን የሰላም፣ የብልፅግናና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ አባላት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው የሀገራዊ ለውጡ ሪፎርም ስራ ሲጀመር ይዞት የተነሳው እሳቤ ጠንካራ፣ ዘመኑን የዋጀ፣ ሀሳብ አፍላቂ አቃፊነት መሆኑን ጠቅሰው ከለወጡ ውጥን ጀምሮ ትፈርሳለች የተባለችን ሀገር በአዲስ እሳቤ በአመራሩና በአባላት ቁርጠኝነት ህዝባችንን አስተባብረን የገጠሙን ፈተናዎች በማለፍ ለውጥ ማምጣት ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።

ብልፅግና ከምንም በላይ ሰው ተኮር የሆነ፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን መደመርን የብልፅግና መዳረሻ ያደረገ ፓርቲ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ቁቡልነት ያለው ፓርቲ መመስረት መቻሉን አብራርተዋል።

ፓርቲው “አዲስ ክልል በአዲስ እሳቤ” በሚል መርህ ክልላችንን የሰላም፣ የብልፅግና እና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ አቅዶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰው በልማትና መልካም አስተዳደር ስብራቶች ላይ የፓርቲው አባላት ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በቀሪው የምርጫ ዘመን ቅቡልነቱ የተረጋገጠ ጠንካራ ፓርቲ፣ ብቃት ያለዉ መንግስትና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዉ በጋራ በመስራት የሕዝቡን ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply